Sunday 21 July 2013

ምሁሩን የት ፈልገህ አጣኸው?

የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ አንዳንድ ችግሮች ቢኖሩበትም የችግሮቹን መነሻዎች ግን በርግጠኝነት ለመናገር ስንቸገር እና መላ ምት የሆኑ አስተያየቶችን ስንሰጥ እንስተዋላለን:: ከነዚህ አስተያየቶች መካከልም በዘላለም ክብረት የተፃፈ ፅሁፍ በዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ አንብበናል:: ዘላለም በፅሁፉ ለመግለፅ የሞከረው የችግሩን መኖር ብቻ ነው:: የችግሩን መነሾ ለመዳሰስ ቢሞክር ኖሮ ፅሁፉን በተወሰነ መልኩ ችግርና መፍትሄ ጠቋሚ ሊያደርገው ይችል ነበር:: ያንን መነሻ በማድረግ የችግሮቹን መንስኤዎች ከማውቀው በመነሳት ለመዳሰስ እሞክራለሁ:: አስቀድሜ ግን ስለትምህርት ስርአቱ ጥቂት ላንሳ:-

የትምህርት ስርአቱ (Education system) ያሉት የትምህርት እርከን እንደሚከተለው የተከፋፈለ ነው
ሀ) የመጀመሪያ ደረጃ (ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል) ይሆንና በ8ኛ ክፍል ክልላዊ መመዘኛ (ፈተና) ይጠናቀቃል::

ለ) መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ (Lower (Junior) Secondary) (ከ9ኛ - 10ኛ ክፍል) ሲሆን በዚህ የትምህርት እርከን ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ቀድሞ በክልላዊ ቋንቋ ሲማሯቸው የነበሩትን ትምህርቶች በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚማሩ ሲሆን በይዘቱም ሆነ በአቀራረቡ ሰፋ እና ጠንከር ያለ ነው:: በዚህ እርከን ውስጥ ያለፉ ተማሪዎች ለማጠናቀቅ ሃገር አቀፍ መመዘኛ ወይም ፈተና ይፈተናሉ::

ሐ) ሁለተኛ ደረጃ (High School)
በዚህ የትምህርት እርከን ውስጥ ሁለት የተለያዩ አቅጣጫዎች አሉ::

   1. የመሰናዶ ትምህርት (ከ11ኛ - 12ኛ ክፍል)
እዚህ የምናገኛቸው ተማሪዎች በ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አመርቂ ውጤት ያመጡት ሲሆኑ በድጋሚ እንደምርጫቸው ወደ ተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበረሰብ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ይሰማራሉ:: ይህንን የትምህርት ደረጃ ያጠናቀቁት በድጋሚ ሌላ ሃገር አቀፍ ፈተና ይወስዱና ያለፉት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመደቡ ያላለፉት ደግሞ ወደሚፈልጉት የትምህርት መስክ (ለምሳሌ ወደ ኮሌጆች ወይም የሙያ ትምህርት) ተሰማርተው ተጨማሪ እውቀት ይዘው ወደስራ ይሰማራሉ::

   2. የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ (TVET)
ወደዚህ የትምህርት መስክ የሚሰማሩት ተማሪዎች በ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አመርቂ ውጤት ያላመጡት/ወይም አምጥተው በፍላጎታቸው የገቡት ሲሆኑ እንደየዝንባሌያቸው ወደሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ ገብተው የሙያ ስልጠና ይወስዳሉ::

መ) የዩኒቨርሲቲ ትምህርት (Higher (tertiary) Education)
እዚህ የሚገቡት ተማሪዎች የመሰናዶ ትምህርትን ያጠናቀቁና በተጨማሪ ሌላ ሃገር አቀፍ ፈተና ወስደው አመርቂ ውጤት ያመጡት ናቸው:: በዚህ የትምህርት ደረጃም ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ በየደረጃው እንዲማሩ ይደረጋል::

ይህ እንግዲህ የትምህርት ፖሊሲው የትምህርት እርከኖች አጠቃላይ ይዘት በአጭሩ ነው:: ሙሉው የትምህርት ፖሊሲው በዘላለም ክብረት ፅሁፍ ላይ ስለተያያዘ ማንበብ ይቻላል:: በተያያዘ አፈፃፀሙንም ለአፍታ አጠር አድርገን እንየው::
የትምህርት ፖሊሲውን ለማስፈፀምና ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ አካላት የየራሳቸው ድርሻ አላቸው:: ከነዚህም ውስጥ:-

ሀ) ትምህርት ሚኒስቴር
ለትምህርት ስርአቱ አጋዥ ፍጆታዎችን የማቅረብ፣ ስልጠናዎችን መስጠት/ማሰጠት እና በቅርብ መቆጣጠር እንዲሁም አፈፃፀሙን መገምገም ወይም ማስገምገም፣ የፖሊሲ ግምገማ በማድረግ ማሻሻያ ካስፈለገ ማድረግ/ማስደረግ የዚህ መስሪያ ቤት ትልቁ ድርሻ ነው::

ለ) የክልል፣ ዞን እና ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤቶች
እነዚህ ባለድርሻ አካላት በየእርከኑ ላሉት የትምህርት ስልጠናዎች፣ የመምህራን ምደባዎች፣ የመምህራን እድገት ውሳኔዎች ሃላፊነት ሲኖርባቸው ለትምህርቱ ጥራትና ብቃት በድጋሚ ወሳኝ አካላት ናቸው::

ሐ) የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን
ለትምህርት ጥራቱ መጓደል ወይም መጨመር ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ:: የመምህራን ክትትል፣ የተማሪዎች ክትትል፣ ከወላጆች ጋር የሚኖርን ግንኙነትና ክትትል በተመለከተ አፈፃፀሙን መገምገም እና አፋጣኝ እርምጃዎችን የመውሰድ ሃላፊነት መወጣት የሚገባቸው ናቸው::

መ) መምህራን
የትምህርት ስርአት የጀርባ አጥንት መምህራኑ ናቸው:: መምህራን በሚያስተምሩት መጠን የትምህርትን ውጤት እንለካለን:: የመምህራን ብቃት ካለም በተዘዋዋሪ የትምህርት ጥራት አለ ማለት ያስደፍራል:: የተማሪዎችም ውጤት በመምህራኑ የማስተማር ብቃት ላይ ያነጣጠረ ይሆናል:: መምህሩ ብቃት እስከሌለው ድረስ የፈለገውን ያህል ጥሩ የሆነ የት/ት ፖሊሲ ወይም አቅርቦት ቢኖር የት/ት ጥራት ሊኖር አይችልም::

ሠ) በዩኒቨርሲቲ ደረጃም ያለው አስተዳደራዊ አካሄድ ከላይ ከጠቀስኳቸው ጋር በተወሰነ መልኩ ስለሚገናኝ አልፌዋለሁ::

  • ታዲያ የትምህርት ጥራቱ ለምን አጠያያቂ ሆነ?
የትምህርት ጥራት የለም የሚል አጠቃላይ መደምደሚያ መስጠት እጅግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው:: ደካማ የሆኑ ተማሪዎች እንዳሉን ሁሉ እጅግ ጠንካራና ምስጉን ተማሪዎችም እንዳሉን መዘንጋት የለብንም:: የሆነ ሆኖ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ላይ ሃሳብ ማንሳት ቢቻልም ለጊዜው ከሁለተኛ ደረጃ አንስቶ ያለውን ለመዳሰስ እንሞክር::

1) የስርዓተ ትምህርቱ ቀረጻ እና አተገባበር
በትምህርት ፖሊሲዉ ንዑስ አንቀፅ 3.1.2. ላይ ሥርዓተ ትምህርት ሲዘጋጅም ሆነ ሲተገበርና ሲገመገም ኀብረተሰቡ በሰፊው የሚሳተፍበት ሥርዓት በመቀየስ በየደረጃው የትምህርት ባለሙያዎችን መምህራንን ቁልፍ የሆኑ የልማትና አገልግሉት ሰጪ ድርጅቶችንና የምርምር ተቋሞችን ቸንዲሁም ተጠቃሚ ኀብረተሰቡን ባቀፈ ሁኔታ ይከናወናል ይላል:: ነገር ግን ይህ የተተገበረው (ባለኝ መረጃ) በቅርቡ ለተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ ላይ ብቻ ነው:: የሚመለከተው የመንግስት አካል የካሪኩሉም ክለሳ ወይም የፖሊሲ ለውጥ ሲደረግ ቢያንስ መምህራንን በስፋት ያካተተ እና በየደረጃው ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ቢሆን የተሻለ ይሆናል:: ጥቂት መምህራንን አሳትፎ ብዙሃኑን ያሳተፈ ማለት ስህተት ነው:: 

2) የፕላዝማ ጉዳይ
መንግስት የትምህርት ፖሊሲዉን ለማስፈፀም ከጀመራቸው ስልቶች ውስጥ አንዱ ትምህርትን ወጥ በሆነ መልኩ በፕላዝማ ቴሌቭዥን አማካኝነት ማስተላለፍ ነው:: መርሃ ግብሩ ሲጀመር መምህሩን እንዲተካው ተደርጎ ሳይሆን መምህሩን እንዲያግዘው አካሄዱም ሃገራዊ ወጥነት እንዲላበስ ታስቦ ነበር:: ነገር ግን በተሳሳተ መንገድ በተሰራጨ አስተሳሰብ ይህ የአፈጻፀም ዘዴ ግቡን እንዳይመታ ተደርጓል:: ለዚህ ተወቃሽ ሊሆኑ የሚችሉት በፖለቲካው መስክ የተሰማሩት የመንግስት ተቃዋሚዎች ናቸው:: ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል የፕላዝማው ትምህርት መምህሩን እንዲተካ ታስቦ እንደተቀየሰ ተደርጎ በመምህራኑ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ለማሳደር ተሞክሯል:: በዚህም የተነሳ በርካታ መምህራን ቸልተኛ እንዲሆኑ የራሱን አስተዋፅዖ አድርጓል::

3) ወጥነት የሌለው የመብራት ሃይል አቅርቦት አለመኖር
የፕላዝማው ፕሮግራም ሲዘጋጅ መብራትን ታሳቢ ያደረገ ቢሆንም ቀጣይነቱ እጅግም አጥጋቢ አልሆነም:: በዚህም የተነሳ መብራት ከጠፋ መምህራን ክፍል ትተው እንዲወጡ ተማሪዎችም ሳይማሩ እንዲዉሉ የተደረጉባቸውን ት/ቤቶ ማጣቀስ ይቻላል:: ጀነሬተር የተገጠመላቸውም ቢሆኑ ውጤታማነታቸው የታሰበውን ያህል አልሆነም:: ነገር ግን ፕሮግራሙ ሲቀረፅ ይህን ታሳቢ ያደረግ ሆኖ መብራት በሚጠፋበትም ግዜ መምህሩ የፕላዝማ ፕሮግራሙ ካቆመበት እንዲቀጥል የታለመ ነበር:: ነገር ግን መምህራን ላይ በተፈጠረው የተሳሳተ አመለካከት የተነሳ በርካታ መምህራን በየቀኑ ሌሰን ፕላን ሳያዘጋጁ እንዲሁም ለትምህርቱ በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ ስለሚመጡ መብራት ሲጠፋ መቀጠል ስለማይችሉ ትምህርቱ ይቋረጣል::

4) የአመራር ብቃት
ይህ ከላዕላይ እስከ ታህታይ ያለውን መንግስታዊ መዋቅር ይመለከታል:: አመራሮች ሲሾሙ ካላቸው ፖለቲካዊ ታማኝነት እንጂ ብቃትን ያገናዘበ እንዲሆን የታለመ አይደለም:: ለዚህ ማሳያ ሊሆን የሚችለው እራሱ ት/ት ሚኒስቴር ሲሆን በውስጡ የያዛቸው ኤክስፐርቶች አብዛኞቹ ማለት በሚያስችል ደረጃ የጅማ እና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ትምህርት ምሩቃን ናቸው:: ይህ ሊስተካከል የሚገባው ሲሆን በትምህርት አስተዳደር መስክ የተመረቁ ለምሳሌ ያህል የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አስተዳደር ምሩቃን ላይ ያነጣጠረ ምደባ ቢደረግ ለውጥ ማምጣት ይቻል ይሆናል:: መንግስት የራሱን ፖለቲካዊ አቅጣጫ ለማስፈፀም በሚኒስትር ደረጃ የሚፈልጋቸውን ሰዎች አድርጎ ኤክስፐርቶችን ግን በሙያው ብቁ የሆኑትን መመደብ ቢችል ችግሮችን በቀላሉ መቅረፍ ይቻላል:: ይህ በክልል፣ ዞን፣ ወረዳ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ሳይቀር አንገብጋቢ ችግር ሆኖ ይስተዋላል:: የአመራር ብቃት ያላቸው መምህራን በርዕሰ መምህርነት ቢመደቡ፣ የተሻለ ብቃት ላስመዘገቡ ምስጋና ቢቸራቸው ውጤታማነቱን ማሳደግ ይቻላል:: ከላይ እንዳልኩት እነዚህ ነገሮችም በከፊል በከፈተኛ ት/ት ዘርፍም ይታያሉ:: ለምሳሌ የሃይል አቅርቦት፣ አመራርን በተመለከተ::

5) የተማሪዎች ቸልተኝነት
ይህ ችግር በየእርከኑ ባሉ በርካታ ተማሪዎች ላይ ይታያል:: ከጥቂት ተማሪዎች በስተቀር ቤተ መፅሃፍትን አዘውትሮ የመጠቀም፣ የትምህርት ግዜን በአግባቡ የመጠቀም ዝንባሌም ከግዜ ወደ ግዜ እየቀነሰ እንደመጣ ለመረዳት ሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶችን ወይም ዩኒቨርሲቲዎችን ማየት ይቻላል:: የከፍተኛ ት/ቱ እንዳለ ሆኖ በየእርከኑ የሚወጡ ተማሪዎችን በተመለከተ በት/ት ፖሊሲዉ ንዑስ አንቀፅ 3.2.8. ላይ እንደተመለከተው ከየሳይክሉ የሚወጡ ተማሪዎች አስፈላጊዉን የሙያ ስልጠና የሚወስዱባቸው ተቋማት እንዲኖሩ እንደሚደረግ ይገልፃል:: በየደረጃውም ከአንደኛ ደረጃ የሚወጡ ተማሪዎች እንደየእድሜያቸው ስልጠና ወስደው ወደ ግብርና፣ እደ-ጥበብና ኮንስትራክሽን በጀማሪ ባለሙያነት እንዲሰማሩ እንደሚደረግና የሌሎቹንም እርከኖች በተመሳሳይ ይገልፀዋል:: ነገር ግን የማሰልጠኛ ተቋማቱ ቁጥር አነስተኛ ከመሆናቸው በተጨማሪ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ወደ ተጠቀሱት የሙያ ዘርፎች ለመሰማራት ያላቸው ተነሳሽነት እጅግ አናሳ ነው::

እንግዲህ ከላይ ባሉት እና ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች ውስጥ ያለፉት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ሊኖራቸው የሚችለውም ተፎካካሪነት እጅግ አጠያያቂ ይሆናል:: አሁን አሁን እያስተዋልን እንዳለነው ይህ ችግር ስማቸውን እንኳ አስተካክሎ ለመፃፍ የሚቸገሩ ተማሪዎች እንዲኖሩን እያደረገ ይገኛል:: የዩኒቨርሲቲ ትምህርት የራሱ የሆነ ድርሻ ቢኖረውም ዋነኛ አላማው ግን ተማሪውን ቀጣይ ለሚሰማራበት የስራ መስክ ብቁ የማድረግ እንጂ ከታች መማር የሚገባዉን ትምህርት ማስተማር አይደለም:: ከስር ጀምሮ እየተበላሸ የመጣው ትውልድ ሲመረቅ ለሚያሳየው ድክመት ዩኒቨሪሲቲዎች ተጠያቂ ሲሆኑም እናስተዉላለን:: ነገር ግን ተጠያቂነቱ በከፊል እንዳለ ሆኖ ትልቁ ድርሻ ያለው ግን ከታች ባሉት የት/ት እርከኖች ላይ ነው:: የስምን አጻጻፍ ዩኒቨርሲቲ እንዲማር መጠበቅ የዋህነትም ነው::

  • ተማሪው ሲመረቅ የት ይግባ?
ይህ በትምህርት ፖሊሲውም ላይ በግልፅ የተቀመጠ ሲሆን ሃገራችን አሁን ባላት አቅም ይህን ሁሉ ምሩቅ ወደ መንግስት ሰራተኝነት የመለወጥ አቅሙ የላትም:: እናም ትውልዱ በትምህርት መስክ ባገኘው እውቀት የራሱን የስራ እድል በራሱ እየፈጠረ መስራት ይጠበቅበታል:: ለዚህ ደግሞ ተማሪዎች የራሳቸውን ልዩ ችሎታ እና ዝንባሌ አውቀዉና ተረድተው እንዲማሩ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ እገዛ ማድረግ የሚገባቸው መምህራን ቢሆኑም ይህንን የሚያደርጉ ጥቂቶች ብቻ ናቸው:: ይህ ባለመደረጉም ተማሪዎች ሲመረቁ የት መቀጠር ወይም ምን መስራት እንዳለባቸው እንዳይረዱ እንቅፋት ሆኗል:: ዝንባሌያቸውንም ሳይረዱት ተመርቀው ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: ዘላለም ክብረት ያነሳትም ተማሪ የሙያ ዝንባሌዋን ባለማወቋ የተነሳም ነው እናቷን ለማስደሰት ብቻ መመረቅን እንደ አላማ አድርጋ የተማረችው:: እንዲህ አይነት ችግሮች የተከሰቱት ወደድንም ጠላንም በመምህራን የስራ ድርሻዎች በአግባቡ አለመፈፀም ነው:: ማስተማር ማለት ተዘጋጅቶ ክፍል መግባት ብቻ ሳይሆን ተማሪውን መንገድ ማሳየት፣ መምራት እና መቅረፅም ጭምር ነው::

  • ኮብል ስቶን ስህተት ነው?
ይህ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚተች የስራ ዘርፍ ነው:: ሆኖም መንግስት የራሱን የስራ ድርሻና እቅድ ከማስፈፀም አኳያ ይህን የስራ እድል ፈጥሮ ስራ ያጣችሁ ተደራጁና ይህን ስሩ ሲል ይስተዋላል:: ይህ በምንም መልኩ ቢታይ ስህተት የለውም:: መንግስት የመሰረታዊ ልማት ዝርጋታን በተመለከተ ያስቀመጠውን ግብ ለማሟላት አሉኝ የሚላቸውን የስራ እድሎች በመፍጠር ሊያሰራ ይችላል:: በየአመቱ ለሚመረቁ በ 2 ወይም 3 አስር ሺህዎች ለሚቆጠሩ ምሩቃን ሃገራችን የስራ እድል ይኖራታል ወይም ትፈጥራለች ብሎ መጠበቅ የዋህነት ይመስለኛል:: ስህተቱ የሚፈጠረው ተማሪው ችሎታዉን እና ዝንባሌውን ሳያውቅ እንዲመረቅ ስለተደረገ "ህክምና ተምሬ ድንጋይ አልጠርብም" ወይም "አካውንቲንግ ተምሬ ድንጋይ አልጠርብም" ወይም "ኬሚስትሪ ተምሬ ኑሮ ዘዴ ሰፈር ለሰፈር እየዞርኩ አላስተምርም " ወደሚል እንዲገባ አድርጎታል:: ይህ የስራ መስክ እንደ አንድ የስራ ዘርፍነት ተከብሮ መያዝ ሲገባው ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ብቻ ተማሪዎች ወደስራው እንዳይሰማሩ ማድረግ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ ሊሆን አይችልም:: "ድንጋይ ለመጥረብ ለምን ይህን ያህል መማር አስፈለገ?" ለሚለውም ጥያቄ በማህበር ከመደራጀት ጋር የሚያያይዘው ነገር ያለ አይመስለኝም:: ሃገራችን በዚህ ሰአት እያፈራች ያለችውን የሰው ሃይል ጥራቱ ቢጠበቅና ተማሪዎቹ ተነሳሽነትን እንዲሁም ዝንባሌን ያገናዘበ ትምህርት ቢማሩ ወደ ጎረቤት ሃገራትም ሄዶ ስራ የማግኘት እድሎችን ማግኘት ይችሉ ነበር:: ከዚህ በተጨማሪ ሃገራችን እየገነባቻቸው ባለችው ትላልቅ ግድቦች ላይ የተማሩ እና የተሻለ እውቀት ያላቸው ምሩቃን በተሻለ ገቢ ሁሉንም አይነት ስራ (የቀን ስራ እያልን የምንጠራውንም ጭምር) እንዲሰሩ ቢደረግ ከስራ ጥራት እና የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ የራሱ ድርሻ ሊኖረው ይችላል:: በየአመቱ ከሚመረቀው የተማረ የሰው ሃይል አንፃር ሲታይ እንደድሮው አካውንቲንግ ተምሮ የቢሮ ስራ ብቻ ወይም የታሪክ ትምህርት ተምሮ አስተማሪነት መቀጠርን ብቻ መጠበቅም የዋህነት ነው::

እናም ዘላለም ክብረት ያነሳቸውን አሳሳቢ ጉዳዮች ለመፍታት እና ፈልጎ ያጣውን ምሁር ለማግኘት ቁልፉ ያለው ከታች ከሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉት መምህራን የተማሪዎቻቸውን የሙያ ዝንባሌ በማወቅ እና እንዲለዩት እገዛ በማድረግ ሃላፊነታቸውን ሲወጡ ወይም እንዲወጡ ሲደረግ ነው:: ከላይኛው እርከን ያሉትም መምህራን ለሰልጣኙ አስፈላጊውን እውቀት በመስጠት ረገድ ያለባቸውን ሃላፊነት በትክክል ሲወጡ ነው:: አመራሩም ፓለቲካን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ከመንግስት ስራ ነጥሎ ማየት ችሎ ለትምህርቱ ልዩ ትኩረት ሲሰጥ ነው:: ምሁሩንም ጠመኔ ወይም ወረቀት ይዞ ብቻ ሳይሆን ድንጋይ እየጠረበ ወይም አካፋና ዶማ ይዞ ወንዞችን እየገደበም ያማረረውን የመብራት ሃይል ችግር ሲያቃልል ወይም ትራክተር እየነዳ ያማረረውን የምግብ እህል ውድነት ችግር ሲዋጋም ልታገኘው ትችላለህና እዛም ፈልገው:: ሳጠቃልል የትምህርት ጥራቱ ጉድለት የአፈጻፀም እንጂ አጠቃለይ የትምህርት ፖሊሲው አይደለም:: የተለየ እይታ ያለው ካለም (ነገር ግን ፖሊሲን ከአፈፃፀም ለይተን) በአንድ ወገንተኝነት ሳያነጣጥር ከነባራዊው ሁኔታ ጋራ እያገናዘብን መፍትሄ ጠቋሚ እንዲሆን እንወያይበት:: የዛሬ ሃያ ወይም ሰላሳ አመት በነበረው የህዝብ ብዛት እና የተማረ የሰው ሃይል ብዛት ጋር እያወዳደርን አዲሱን ትውልድ ለሙያ ፍቅር እንዳይኖረው ባናደርግ እንዲሁም ዝንባሌውን ለይቶ እንዳያውቅ መጋረጃ ባንፈጥርስ? አበቃሁ!!!

ይህ ፅሁፍ በ 09 July 2013 Zone9 ብሎግ ላይ ቀርቦ የነበረ ነው::


Tuesday 16 July 2013

I Believe this is Exactly what had Happened

Zimmerman (if)                               Trayvon (if)
 
Since George Zimmerman was not wearing any security uniform, to the young black boy, all he could see in this heavy built white man was nothing but all the signs of a stalker. And for George Zimmerman to stalk him like that was simply to scare him so that the boy may not come to that neighborhood again. The case is about a fight that went out of control. It was not Zimmerman’s intention to kill the young boy simply because he was black. The killing was totally accidental.

The little black boy was scared for his life when this white man was stalking him. When the boy walked faster, the stalker walked faster and faster. The white boy was told to stop by the police. But, because he had confidence on his gun, he harassed him anyways. Then young boy became nervous, turned over and attacked the white man in self-defense. The white man fell to the ground and screamed for help. The black boy banged the head of the white boy against the ground. As his head was being banged against the ground, the white boy pulled out his gun to just scare the boy. But, instead, he shot him by accident.

I believe, the whole fight took place within 10 seconds.

George Zimmerman said that Trayvon Martin was trying to take the gun away from him. But, that is a lie. May be he thought if he just pulls his gun out to scare the boy, the boy would fight for that gun. I believe, the boy would have been scared and stopped the fighting.

The Medical Examiner testified that “the bullet went from the front to the back of the teen’s chest, piercing his heart.” Zimmerman was right when he said that he was at the bottom and Travon was on the top. Zimerman shot him right on his chest, while the boy’s two hands were holding his shirt and banging Zimerman’s head against the ground.

Trayvon’s two hands were holding Zimerman’s neck as he banged him against the ground. He has to have a third hand to try to take the gun away from Zimmerman.

I believe, the reason Zemerman stalked a young black boy is because of his race. If he was white, he would not stalk him.

The outcome of the verdict would also be different if the victim was white and the shooter was black.

Friday 12 July 2013

Customer Care or Spying?


Operator : Thank you for calling Pizza Hut. May I have your…

Customer : Hello, can I order..

Operator : Can I have your multi-purpose card number first, Sir?

Customer : It s eh…, hold………. on……889861356102049998-45-54610

Operator : OK… you’re Mr Singh and you’re calling from 17 Jalan Kayu. Your home number is 4094! 2366, your office 76452302 and your mobile is 0142662566. Which number are you calling from now Sir?

Customer : Home! How did you get all my phone numbers?

Operator : We are connected to the system Sir.

Customer : May I order your Seafood Pizza…

Operator : That’s not a good idea Sir.

Customer : How come?

Operator : According to your medical records, you have high blood pressure and even higher cholesterol level Sir

Customer : What?… What do you recommend then?

Operator : Try our Low Fat Hokkien Mee Pizza. You’ll like it.

Customer : How do you know for sure?

Operator : You borrowed a book entitled Popular Hokkien Dishes from the National Library last week Sir.

Customer : OK I give up… Give me three family size ones then, how much will that cost?

Operator : That should be enough for your family of 10, Sir. The total is $49.99!

Customer : Can I pay by! credit card?

Operator : I’m afraid you have to pay us cash, Sir. Your credit card is over the limit and you owe your bank $3,720.55 since October last year. That’s not including the late payment charges on your housing loan, Sir.

Customer : I guess I have to run to the neighborhood ATM and withdraw some cash before your guy arrives.

Operator : You can’t Sir. Based on the records, you’ve reached your daily limit on machine withdrawal today.

Customer : Never mind just send the pizzas, I’ll have the cash ready. How long is it gonna take anyway?

Operator : About 45 minutes Sir, but if you can t wait you can always come and collect it on your motorcycle…

Customer : What!

Operator : According to the details in system ,you own a Scooter,…registration number 1123…

Operator : Is there anything else Sir?

Customer : Nothing.! .. by the way… aren’t you giving me that 3 free bottles of cola as advertised?

Operator : We normally would Sir, but based on your records you’re also diabetic…….

Customer : #$$^%&$@$%^

Operator : Better watch your language Sir. Remember on 15th July 1987 you were convicted of using abusive language on a policeman…?

Customer : Faints…..

Wednesday 3 July 2013

የአርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ወንድም ዶ/ር ያዕቆብ አስታጥቄ የ2013 የአሜሪካ ምርጥ መምህር ተብሎ ተመረጠ::

 የአርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ወንድም ዶ/ር ያዕቆብ አስታጥቄ የ2013 ምርጥ መምህር ተብሎ ተመረጠ::
“2013 ASEE National Outstanding Teaching Award” Winner
“2012 ASEE Mid-Atlantic Distinguished Teacher Award” Winner
Short Biography
Dr. Yacob Astatke completed both his Doctor of Engineering and B.S.E.E. degrees from Morgan State University (MSU) and his M.S.E.E. from Johns Hopkins University. He has been a full time faculty member in the Electrical and Computer Engineering (ECE) department at MSU since August 1994 and currently serves as the Associate Chair for Undergraduate Studies. Dr. Astatke is  the winner of the 2013  American Society for Engineering Education (ASEE) “National Outstanding Teaching Award“. This award covers 340 engineering schools and close to 27,000 engineering faculty members (i.e. teachers) from all 50 states. Dr. Astatke is also the winner of the 2012  American Society for Engineering Education (ASEE) “Mid-Atlantic Region Distinguished Teacher Award.” The Mid-Atlantic division includes engineering schools from 6 states :Maryland, Washington DC, Delaware, Pennsylvania, New Jersey and New York.
Dr. Astatke teaches courses in both analog and digital electronic circuit design and instrumentation, with a focus on wireless communication. He has more than 15 years experience in the development and delivery of synchronous and asynchronous web-based course supplements for electrical engineering courses. He has published over 40 papers and presented his research work at regional, national and international conferences. He also runs several exciting summer camps geared towards middle school, high school, and community college students to expose and increase their interested in pursuing Science Technology Engineering and Mathematics (STEM) fields. Examples are the “Rube Goldberg Engineering Design” camp funded by Innovative STEM Solutions (ISTEMS) in collaboration with Arizona State and Purdue University, the “Balloon Satellite Payload Design” camp funded by the Maryland Space Grant Consortium and NASA in collaboration with University of Maryland at College Park, and the “Smart Lighting Engineering Research” camp funded by the National Science Foundation (NSF) in collaboration with Rensselaer Polytechnic Institute (RPI), Howard University and Boston University. He is also the founder (in 2000) and Director of the “Foundations of Mathematics” summer program, which is a 5 week online summer math course offered for FREE to all pre-freshman engineering students admitted to the university.
Dr. Astatke has been travelling to Ethiopia for the past 10 years to teach graduate
courses, or provide training and guest lectures. For the past four years, he has donated laboratory equipment, and has been providing training  related to the use of the Mobile Studio Technology and pedagogy in the ECE department of five universities in Ethiopia : Addis Ababa Institute of Technology (AAiT), Hawassa University, Debre Berhan University, Bahir Dar University and Jimma University (Read the report attached here for more information.) He is currently working with the Global Engineering Dean’s Council (GEDC)and the International Federation of Engineering Education Societies (IFEES) to expand his effort throughout Africa (Read the report attached here for more information).