በአሌክስ አብርሃ
ቤቲ አበራ አሳምራ ትወክለናለች!! ተንጫጫን ፣ ተሳደብን ፣ አሸሞርን እናም ረገምን!! አንዳንዶችም ከእናንተ ሃፂያት የሌለበት ይውገራት ሲሉ ስለቤቲ
በፌስቡክ ወልጣ ቀኝ መስቀል ላይ ተሰቀሉ በ‹ኮሜንት ጅራፍ አርባ ተገረፉ በ‹ኮሜንት› ችንካር ተቸነከሩ! እኔም
ስቀሏት እያልኩ ያውም ፊት ላይ ቁሜ ስጮኽ ሰነበትኩ ትላንት ታዲያ ቆም ብየ ‹‹ሴቶች ስለሚደብሩኝ ነው ወይስ
የልጅቱ ስራ አበሳጭቶኝ እንዲህ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገርኩት›› ብየ አሰብኩ፡፡( ውይ እናገራለሁ እንጅ ሆዴ እኮ የዋህ ነው) እስቲ ከምር እንነጋገር ቤቲ እኮ አሳምራ ነው የምትወክለን!! የደረስንበትን የማህበረሰብ ዝቅጠት የሞራል ውድቀት እና ርኩሰት ‹‹አፈር ስሆን ባይጥምም …›› ብላ በአፍ ባፋችን አጎረሰችን ቤቲ እህታችን ምሳሌያችን …. እኛው በግድፋችን ሙሉ
የማህበረሰብ ወጣችን ላይ የዘነቅነውን ወጥ ያቀመሰችን ማማሳያ ናት ቤቲ! እንጀራውማ ያለው እዚሁ ያንተው መዲና
ላይ ነው ለስብሰባ የመጣው ሁሉ እየጠቀለለ የሚጎርሰው …..!! ማን ፈጠራት እችን ልጅ እኛው! ማን አሳደጋት እኛው
! አራዳ ሁኝ ብሎ ማን መከረ እኛው !(የተበላሸ ና የተንጋደደ ባህልና የጠፋ ረትውልድ ኢንጅነሮች እኛው) ዋናው
ነጥብ እች ልጅ ምን ፈልጋ ሄደች መቸም ወሲብ አምሯት የካሳንችሷ ልጅ ደቡብ አፍሪካ ዘመተች አንልም! ብር!! ብር
!! ብር!! ብር ፈልጋ ቋንጣ እንዳየ እረሃብተኛ ድመት ዘለለች ከስር ቋንጣዋን ፈላጊ ውሻ ጠበቃት ተያይዘው
ወደቁ!! አወዳደቃቸውን ባለቋንጣወቹ አሳዩን!! ሆዳም አልናት እዚሁ ምድራችን ላይ ሴቶቻችን እንደጥሬ ስጋ ሲዘለዘሉ
አፋችንን እንዳልዘጋን!! ታዲያ ለብር ብለን ምን ያላደረግነው ነገር አለ …ይሄው የህዝብ ገንዘብ ሙጥጥ ያደረጉት
ሙሰኛ ባለስልጣናትህ ለብር ስራቸው ከማመንዘር ምን ይተናነሳል …አንተው አይደለህ ዋው እያልክ እርቃን ስታደንቅ
የነበረው ዛሬ አለም ሲያይህ ምን አስደነበረህ…. ዘፋኞችህ የፊልም ባለሙያ ተብየወችህ ሲራቆቱ ሲዳሩ ስታይ
አልኖርክም …ዛሬ ምን አንገበገበህ…..
ወደድንም ጠላንም አለም አይቶናል! አትወከወለንም እያልን ብንዘል ብንፈርጥ ምንም አናመጣ የሆነውን ነው ያሳየችው ! ከዳር እዳር ከገጠር እስከከተማ ቁርጥ ቤቲን ነን!! ዝሙትን ከሃይማኖቱ በላይ የሚያመልክ መሃበረሰብ ፈጥረናል ለሳይንስና ቴክኖሎጅ እንደመቃብር መርግ የተጫነው አይምሯችን ለወሲብ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ይበራል ዳዴ የምትላት ህፃን እጇን ነጥቃህ ወደወሲብ ስትሮጥ ተማር ያልከው ልጅህ ወንድምህ የሴት እግርና መቀመጫ ላይ በምርቃና አይኑን ሲያጉረጠርጥ… አንተስ ራስህ ብትሆን ማነህ በቃ ወሲብ ላይ ነው ፍጥነታችን….. በአጼ ቴውድሮስ ዘመነ መንግስት የተጀመረው የጋፋት ኢንዳስትሪ ከመቶ ምናምን አመት በኋላም ስንዝር አልተራመደም ….በአጼ ሚኒሊክ የተጀመረው መብራት ይሄው ዛሬም ድረስ ግማሹን አገራችንን እንኳን አላዳረሰም ዛሬም በኩራዝ የሚጨናቦሰው የትየሌ ነው!ገጠሩን ተወው እዚህ መሃል ከተማው ላይ አስር ጊዜ ድርግም ሲል ታየዋለህ ! ስንቱን ልንገርህ መሬት ላራሹ ስንል የነበረው መቸ ነው….አድዋ ላይ ቅኝ ግዛትን እንቢ ካልንስ ስንት ዘመን ሆነን ዛሬም ግን ዲሞክራሲ ባንድ ጀምበር አይመጣም እያልን ስንት ጉድ ጀምበር ሸኘን…..አየህ ለዚህ ሁሉ ስልጣኔ ድርግም አድርገን የዘጋነውን አይምሯችንን ለወሲብ በረገድነው ኤች አይ ቪ ትላንት ብቅ ብሎ ዳር እስከዳር አመሰን ፈጀን ጫት ትላንት ተከስቶ የማሽላ እርሻህን ቀማህ ገና የጤፍ ማሳህን ይነጥቀሃል!! (በአንድ ጀምበር ጀምበርህና ጀምበሬ ለክፉ ሲሏት እንደእያሱ ፀሃይ ትቆማለች ) ….አቤት ኤች አይ ቪ መንገድ ብትሆን መብራት ብትሆን ዲሞክራሲ ብትሆን ……ምን አገናኘው ትል ይሆናል ….ለወሲብ ያባከንከውን ጊዜ ቁጭ ብለህ አስላው …በአገርህ ወንዶች አባዛው አየህ ….አገርህ ያጣችው ጊዜ……አንተ ያጨድከው እድሜ….ሴቶችህ የበሰበሰ የፍቅር ዲስኩር እያወሩህ አንተም በየሄድክበት ቀበቶህን እየፈታህ ዘመንህን ፈጀህ…..ድሃ ሆንክ በድህነትህ ላይ ተረታም ኮተታም ዝሙታም ሆንክ …. ለምን ይመስልሃል ቁጥርህ እንደምድር አሸዋ የበዛው አግብተህ በክብር ከወለድከው በየሜዳው የፈለፈልከው ይበዛል 80 ሚሊዮን ትላለህ በኩራት ! ከእጅ አይሻል ዶማ አሉ ሸክም!! አንድ ሚስኪን የምንግስት ሰራተኛ በነተበ ጅንስ ሱሪ በተንሻፈፈ ጫማ እየፈጋ ስንት ቤተሰብ ያስተዳድራል የምትቆጠረው ግን አንተ ነህ! ቤቲ አገራችንን አሰደበች…..ኪኪኪ
አገራችን እራሷ ለጨጫ ስንዴ ቀሚሷን የትም አልገለበችም እንዴ ….የጦር መሳሪያ እንዲመፀወታት የሶሻሊዝም አልጋ ላይ አልተንከባለለችም እንዴ ….አረብ አገር ብትል አንገታቸው ላይ የተደቀነ ሰይፍ ንቀው በየማጀቱ በሴተኛ አዳሪነት የሚኖሩ እኛንም የሚያኖሩ የነማን ሴቶች ናቸው ተው ባክህ እስኒከርህ ይመስክር ያንከረፈፍከው ሞባይል አፍ አውጥቶ ይናገር ስንትህ ነህ እህትህ ሃብታም ‹‹ጠበሰች›› ብለህ ስእለት የምታስገባ ስንትህስ ነህ እህትህ ሚስኪን በመውደዷ ቤተሰብ ተደፈረ ብለህ የምትደነፋ….. የማንም ሽማግሌ ቅምጥ አድርጎ የሚጫወትባቸው የነማንን እህቶች ነው …. ወላ ቄስ ወላ ፓስተር ወላ ሸህ …. የምትባል ሁሉ (ብዙሃንህ) ተደብቀህ ፆለት ታውጃለህ ሰብስበህ እግዚዮ ታስብላለህ …የቤተ እምነትህን አጥር ተደግፈው በየምሽቱ በወሲብ እሳት የሚቃጠሉ ስንቶች ናቸው አልሰማህም ፓስተር አልሰሙም መምሬ….ሸሃችን …ኧ……. መስጊድ ፈረሰብኝ የቤተ ክርስቲያን አጥር ተነካብኝ ብለህ የነፃነት ታጋይ ልትሆን የሚዳዳህ ሁሉ ትውልድ በወሲብ ወላፈን ሲጠራረግ ቃል ተንፍስሃል ….የታለ ፈጣሪ የሰጠህ አደራ እረኛ ነኝ ትላለህ ግልገሎችህ የትምህርት ቤት ደንብ ልብሳቸውን ግጥም አድርገው ጫት ቤት ሲኮለኮሉ ፊት ለፊት ተው ያልከው መቸ ነው? በሰው ውድቀት ስብከት እያዘጋጀህ መድረክህን ታሳምራለህ ቤተ እምነትህ ውስጥ ታጉረህ እርስ በእርስህ ‹‹አሚን ›› ከመባባል ውጣ መጠጥ ቤት ይዘጋ በል ….ጫት ቤት ትውልድ ገደለ በል…. ይሄ ሁሉ ወጣት የሚያወጣው አጥቶ ሲባክን አታይህም…ሴቱ እርቃኑን ሲባዝን የውድድርና የቁሳቁስ አዙሪት ውስጥ ገብቶ ቦረሳውን አንጠልጥሎ ከተማ ሲያካልል … ሽማግሌው ክብሩን ጥሎ አንድ ፍሬ ተማሪ በመኪናው አፍኖ ሲወስድ አፍህን በመዳፍህ ሸፍነህ ‹‹ጉድ››እንድትል ነው ፈጣሪ ስልጣን የሰጠህ ? ተናገር የተሸከምከው መፀሃፍ እንደዛ ነው የሚልህ የእያንዳነዱን ሰው ደም ከእጅህ ይፈልጋታል ማን ይድረስለት ይሄን ወጣት..በየሽርኩቻው ተደብቀህ ስለዘመርክ ህዝብ አይድንም መንግስትን ትውልድ የሚያልቀው ለምን በለው ! በየቤትህ በቴሌቪዥን …ውስጥ ልብሷ የሚታይ ሴት መቀመጫዋን እስካፍንጫህ አስጠግታ ስታወዛውዝብህ ስትገለፍጥ እያመሸህ ቀን ትደሰኩራለህ….
መስጊድና ቤተ ክርስቲያንህ ቀን ማታ ርግብ ሰፍሮበት እየዋለ የዝሙትና መጠጥ ቤቱ በሰው ተሞልቶ በሰይጣን እቅፍ ሲያረግድ የሚያመሸው ማን መሰለህ ፈጣሪ አደራ ያለህ አንተን እረኛ ያደረገለት ትውልድ ነው! ለመስቀል በቴሌቪዥን መስኮት ተኮፍሰህ ‹‹ኢለኒ መስቀሉን ለማግኘት እጣን አጭሳ ….››ትላለህ ትውልድ በኤች አይ ቪ አግርህ ስር አየጨሰ ….እጁ ላይ ያለውን ቃል ማንበብ ተፀይፎ ለራሱ መቃብሩን እየቆፈረ ላለ ትውልድ መስቀል ቆፍራ ስላገኘች ፃዲቅ ብታወራው የሚሰማህ ይመስለሃል ….እዚህ እንጦጦ ማሪያም ታቦት ለማንገስ ወገቤን የሚልህ ወጣት ነው ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሂዶ ገመናህን ሲዘከዝከው የምታየው አዎ ትወክለናለች!! …..እና ማሪያም ታማልዳለች አታማልድም ክርክርን እኔን ካልተከተልክ እሳት በላህ መቃብር ተፋህ…. ማስፈራሪያህን ንትርክህን ተወውና ትውልድ ይዳን በል ሰው ወደእንስሳነት አይውረድ በል ….ሲድን ሰው ሰው ስትሸተው ያኔ አምላክህን ይከተላል ! ካልሆነ ግን በአንተ ሃይማኖት ወንበር ላይ ተቀምጦ ሰይጣንን ሲጋብዝ ታየዋለህ እያየኸውም ነው!! እች ልጅ አብግናናለች አትጠራጠር ነገ የማሪያምህን ምስል ከሚያከብረው በላይ የዚችን ልጅ ምስል በተኮላተፈ እንግሊዝኛው የሚያደንቅ ትውልድ ታያለህ አሁንም እያየህ ነው ! ነዋ! ማሪያም የምትወክለው ጨዋ ደናግላንን ነው ….ቤቲ ግን ብዙሃኑን …..ያልቻለ ወደሚመስለው ይሮጣል ……ትወክልሃለች አለም ያየው በትክክል ኢትዮጲያን በተለይም የአዲስ አበባ ሴቶችህን ነው!! አንተ ብትንጫጫ እዝሁ ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ የመጣው ጉሬላ ሁሉ ሴቶችህን ያውቃቸዋል ‹‹ እች ምን አላት›› እያለ ነው ያንተን ቤቲ የሚያያት ……የቁንጅና ውድድር እየተባለ ሴቶችህ ለዝሙት ሲቸረቸሩ አትጮኽም ነበር …. ፈረንጅ እረገጠው በተባለው ቦታ ሁሉ ሴቶችህ ተብረቅርቀው ሲያነፈንፉ ምን አልክ….ስራ የሚያስከብር የሚያኮራ ወንድ የሌለበት አገር የሚያስከብሩ የሚያኮሩ ሴቶች አይፈጠሩም ….ትላንት ልጅነቷን መጠህ ያገባኛል ብላ ስትጠብቅህ የወረወርካት ሴት ናት ዛሬ ታሪክን ምናምንህን ባደባባይ የወረወረችልህ……ሲጀመር ለመናገር ሞራሉ የለህም!! ያላከበርካት ሴት አታከብርህም ያላከበረችህን ሴት ቦታ አትሰጥም ገንፎ ለገንፎ ተያይዞ ዘፍ …..ደቡብ አፍሪካ ላይ!! የዘራሃትን እያጨድክ ነው….ሚሊየን ቤቲወችን ወሲብ አስተማርክ … ሱስ አስተማርክ የሌላትን ትልቅ ነሽ እያልክ የወሲብ ዛርህን ለማርካት አዳነክ አንተ ያገኘኸውን አግኘተህ ዞር ስትል በባዶ ሰብእና የሚኮፈሱ ማን አለብን ባይ ባዶ ሴቶች ከተማህን ሞሉት በእንግሊዝኛ እየተቅጨለጨሉ …..ወንድም መከታ ስላልሆንካቸው ሚሊየኖች አረብ አገር ጎረፉ ….ዛሬም ውይ ሴት እያልክ እኔም እያልኩ አለን ….አምልጠውሃል ሴቶችህ !! ከስር የሚወጡትን አክብር ወላ አስተማሪ ወላ ሃኪም ወላ ሹፌር ወላ ፖለቲከኛ ሰው የሆኑ ሴቶች ተጠራርገው ሰውነት ብቻ የሆኑ ግኡዝ አሻንጉሊቶች በመፍጠር የአንተም እጅ አለበት አትንጫጫ ባክህ ……ቤቲ የሰራችው እዚህ አፍንጫህ ስር የተለማመደችውን ነው በእንቁላሉ በቀጣሽኝ አለ……ሽወች አሉልህ ተመልከት ዙሪያህን ቁጭ ብለህ ምን እናድርግ በል …ከእያንዳንዱ ተልካሻ ክሊፕ ጀርባ ያለ የዝሙት የሱስ አይነት ይደንቀሃል ….ያገባሃል ለምን በል …..ተው በል ….ዝም ካልክ ግን …አሁንም ዝም በል!! እንከዋን ሴራሊዮናዊ ከሌላም አለም የመጣ ፍጥረት ቢያገኙ ሴቶችህ ሲጎርፉ ታያለህ አንተ የለህም ብቃት የለህም ብር የለህም ፀባይ የለህም ….ተረት ብቻ ሴቶችህ ተረትህ ሰለቻቸው ቻው ብለውህ ‹በካት ዎክ…›› ቀጭ …ቀጭ….ቀጭ……ባይ ሃኒ……….
No comments:
Post a Comment