Tuesday 11 June 2013

አያ ጅቦም ኮንዶሚኒየም ስጡኝ አለ?


 

ይህ እውነተኛ ዘገባ ሲሆን የተፈፀመውም አዲስ አበባ ውስጥ ነው:: በትናንትናው እለት በቦሌ አያት አካባቢ ከሚገኙት ኮንዶሚኒየም ቤቶች መሃል በአንደኛው ሁለተኛው ፎቅ ኮሪዶር ላይ ተኝቶ ጠዋት ላይ የተገኘው ጅብ ነዋሪዎቹን አላስወጣ ብሏቸው አርፍዷል:: የሁለቱን የፎቁን ደረጃዎች እንዴት እንዳለፈ አነጋጋሪ የሆነው አያ ጅቦ ረፋዱ ላይ ነዋሪዎቹ ባመለከቱት መሰረት ፓሊስ ደርሶ ሊገለው ችሏል:: አይ አያ ጅቦ!!! ዋነኞቹ ሲታሰሩብህ አንተው ብቅ አልክ?

No comments:

Post a Comment